የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
K / k በላቲን አልፋቤት አሥራ አንደኛው ፊደል ነው።
ግብፅኛ /ደ/ |
ቅድመ ሴማዊ ካፍ |
የፊንቄ ጽሕፈት ካፍ |
የግሪክ ጽሕፈት ካፓ |
ኤትሩስካዊ ኽ |
ላቲን ኽ | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|
|
የ«K» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ካፍ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የዕጅ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ ግን የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች ሥርዓት ለድምጹ /ደ/ ጠቅሞት ነበር።
የካፍ ቅርጽ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ካፓ" (Κ κ) ደረሰ። በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ከ» («ካፍ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ካፍ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'K' ዘመድ ሊባል ይችላል።